
ረብሐ ግሥ
ይህ የግሥ ዓይነት ዘማች ግሦችን ከቀዳማይ አንቀጽ ጀምሮ እስከ አርእስት እና ከዚያ በላይ ያሉትን ቅጽሎችን የሚያገሰግስ ማለት ነው፡፡ (ቀዳማይ አንቀጽን ማርባት/መተንተን ማለት ነው)
by Unknown —9 min read
ረብሐ ግሥ፡- ይህ የግሥ ዓይነት ዘማች ግሦችን ከቀዳማይ አንቀጽ ጀምሮ እስከ አርእስት እና ከዚያ በላይ ያሉትን ቅጽሎችን የሚያገሰግስ ማለት ነው፡፡ (ቀዳማይ አንቀጽን ማርባት/መተንተን ማለት ነው)
መራኁተ ግሥ፡- እነዚህ ደግሞ የፊደላት ዓይነት ሲሆኑ ሁልጊዜ በግሡ መጀመሪያ ላይ የሚገኙ ናቸው። መንሥኤ ግሥ ወይም አርኃውያን ተብለው ይጠራሉ። ግሥ የሚያስነሱ ቀለማት ተብለውም ይጠራሉ፤ እነዚህም፡-
ግእዝ ራብዕ ኃምስ ሳድስ እና ሳብዕ ናቸው።
ምሳሌ፡- ግእዝ—-ቀተለ፣ ቀደሰ፣ ተንበለ
ራብዕ—-ባረከ፣ ማህረከ
ኀምስ—-ሴሰየ
ሳድስ—-ክህለ
ሳብዕ—-ጦመረ ናቸው፡፡
መሠረታዊ ግሥ (ዘማች ቀዳማይ አንቀጽ) ተመሥርቶ የሚገኘው በሦስተኛ መደብ ወንድ ነጠላ ቁጥር ነው (ውእቱ)፡፡
ግሥ የማያስነሱ ቀለማቶች ሁለት ናቸው፤ ማን ማን ናቸው ቢሉ ካዕብ እና ሣልስ ናቸው።
ምሳሌ፡- ሖረ ቴሀ ይላል እንጂ ሑረ ቲሀ አይልም፡፡
የግሥ መድረሻ ቀለማቶች ሁለት ናቸው፤ እነዚህም ግእዝ እና ኃምስ ናቸው። የግእዝ ማስረጃ ከሀ እስከ ፐ የሚገኙ ግሦች በሙሉ ናቸው። የኃምስ ግን አንድ ይቤ ብቻ ነው፡፡ ይቤማ ነባር አንቀጽ አይደለም ቢሉ ካልአዩን፣ ዘንዱን፣ ትእዛዙን ይዞ ስለተገኘ ነው። የረብሐ ግሥ ዓይነቶች
ግሥ የሚረባበት ሁለት ዓይነት መንገድ አለው። እነዚህም፡
ሀ. የዋህ ረብሐ ግሥ
ለ. መሠሪ ረብሐ ግሥ ናቸው፡፡
ሀ. የዋህ ረብሐ ግሥ
ግሥን በውእቱ ባለቤትነት (ዘማች አንቀጽ በውእቱ ስለሚጠሩ ስለሚመሠረቱ) በመራሕያን ባለቤትነት በግሥ አርስቶች ተመሥርቶ መገሰስ /ማገስገስ/ የዋህ ረብሐ ግሥ ተብሎ ይጠራል።
መሠሪ ረብሐ ግስ:-መሠሪ ግሥ የሚረባበት የርባታ ስልት መሠሪ ረብሓ ግሥ ይባላል፡፡ መሠሪ የሚል የስያሜ ቅጽል የተቀጸለበትም ምክንያት የግሥ መደበኛ ዘር በባለቤት ዝርዝር ላይ ሎቱን፣ ቦቱን ፣ የተሳቢ ዝርዝርን እየጨመረ በበጎ እና በክፉ ነገር ስለሚነገር /ስለሚተረጎም/ ነው።
መራኁተ ግሥ፡- እነዚህ ደግሞ የፊደላት ዓይነት ሲሆኑ ሁልጊዜ በግሡ መጀመሪያ ላይ የሚገኙ ናቸው። መንሥኤ ግሥ ወይም አርኃውያን ተብለው ይጠራሉ። ግሥ የሚያስነሱ ቀለማት ተብለውም ይጠራሉ፤ እነዚህም፡-
ግእዝ ራብዕ ኃምስ ሳድስ እና ሳብዕ ናቸው።
ምሳሌ፡- ግእዝ—-ቀተለ፣ ቀደሰ፣ ተንበለ
ራብዕ—-ባረከ፣ ማህረከ
ኀምስ—-ሴሰየ
ሳድስ—-ክህለ
ሳብዕ—-ጦመረ ናቸው፡፡
መሠረታዊ ግሥ (ዘማች ቀዳማይ አንቀጽ) ተመሥርቶ የሚገኘው በሦስተኛ መደብ ወንድ ነጠላ ቁጥር ነው (ውእቱ)፡፡
ግሥ የማያስነሱ ቀለማቶች ሁለት ናቸው፤ ማን ማን ናቸው ቢሉ ካዕብ እና ሣልስ ናቸው።
ምሳሌ፡- ሖረ ቴሀ ይላል እንጂ ሑረ ቲሀ አይልም፡፡
የግሥ መድረሻ ቀለማቶች ሁለት ናቸው፤ እነዚህም ግእዝ እና ኃምስ ናቸው። የግእዝ ማስረጃ ከሀ እስከ ፐ የሚገኙ ግሦች በሙሉ ናቸው። የኃምስ ግን አንድ ይቤ ብቻ ነው፡፡ ይቤማ ነባር አንቀጽ አይደለም ቢሉ ካልአዩን፣ ዘንዱን፣ ትእዛዙን ይዞ ስለተገኘ ነው። የረብሐ ግሥ ዓይነቶች
ግሥ የሚረባበት ሁለት ዓይነት መንገድ አለው። እነዚህም፡
ሀ. የዋህ ረብሐ ግሥ
ለ. መሠሪ ረብሐ ግሥ ናቸው፡፡
ሀ. የዋህ ረብሐ ግሥ
ግሥን በውእቱ ባለቤትነት (ዘማች አንቀጽ በውእቱ ስለሚጠሩ ስለሚመሠረቱ) በመራሕያን ባለቤትነት በግሥ አርስቶች ተመሥርቶ መገሰስ /ማገስገስ/ የዋህ ረብሐ ግሥ ተብሎ ይጠራል።ይ መልተው በካልአይ የሚጎድሉ ግሦች ሁለት ናቸው። እነዚህም ወሀበ እና ክህለ ናቸው። እነዚህም ግሦች ኅርመት ይባላሉ። አወራረዳቸውም ወሀበ-ሰጠ ብሎ ይሁብ-ይሰጣል፣ የሀብ-ይሰጥ ዘንድ፣ የሀብ-ይስጥ ይላል። ክህለ-ቻለ ብሎ ይክል-ይችላል፣ ይክሀል-ይችል ዘንድ፣ ይክሀል-ይቻል ይላል። እነዚህ ግን በአራቱ አዕማድ ሲገቡ ያጎደሉትን ቀለም ያስገኛሉ። ይኽውም ተውህበ ይትወሀብ ይትወሀብ እንደሚለው ነው፡፡
የቆመ ቤቶች ሳድስ ቅጽላቸው በመካከል ሳድስ ” ው”ን አምጥተው ይወጣሉ። ይህም ከሌሎች የተለየ ነው። ለምሳሌ የቀደሰ ሳድስ ቅጽል ቅዱስ ነው። “ዱ” ካዕብ ነው። ቆመ ብሎ ቅውም ሲል ግን “ው” ሳድስ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።
‘ኀሠሠን’ የመሰሉ ግሦች በብዙ በካልአይ በዘንድ እና በትእዛዝ አንቀጽ፣ በአንድ ወንድና በአንድ ሴት ዝርዝር ያጎድላል። ለምሳሌ “ነበበ-ተናገረ” ይላል። በብዙ ነበብክሙ-ተናገራችሁ ይላል። በካልአይ “ትነቡ-ትናገራላችሁ” ይላል ማለት ነው። በትእዛዝ አንቀጽ ደግሞ “ንቡ-ተናገሩ” ይላል። ተጨማሪ ምሳሌ “ኀሠሠ” ን ብንመለከት። በብዙ “ኀሠሥክሙ-ፈለጋችሁ” ይልና። በትእዛዝ አንቀጽ “ኅሡ-ፈልጉ” ይላል። ‘ኀሠሡ-ፈለጉ’ ይልና በትእዛዝ “ይኅሡ-ይፈልጉ” ይላል። በአንዲት ሴት ደግሞ በዝርዝር ኀሠሠቶ-ፈለገችው ብሎ በካልአይ አንቀጽ “ተኀሦ-ትፈልገዋለች” ይላል።
የንባብ ተገብሮ የትርጓሜ ገቢር የሚሆኑ ግሦች አራት ናቸው። እነዚህም “ተለቅሐ-ተበደረ፣ ተመጠወ-ተቀበለ፣ ተጸገወ-ተሰጠ፣ ተወክፈ-ተቀበለ” ናቸው። የእነዚህም አድራጊዎቻቸው “ለ”ን ይሻሉ። ሁለቱም ግእዝ ይስባሉ። መጠወ/ጸገወ/ለቅሐ ወርቀ ለነዳይ ይላል።
የንባብ ገቢር የትርጓሜ ተገብሮ የሚሆኑ ግሦች አራት ናቸው እነዚህም ሐመ-ታመመ፣ ደወየ-ታመመ፣ ጸምአ-ተጠማ፣ ርኅበ-ተራበ ናቸው።
የንባብ አስደራጊ የትርጓሜ አድራጊ አለ። ምሳሌ:- አስደራጊ አፍቀረ-ወደደ:አስወደደ፣ አእመረ-አወቀ:አሳወቀ የሚሉት ናቸው።
የንባብ አስደራጊ የትርጓሜ አድራጊ፣ ተደራጊ፣ አስደራጊ አለ። ምሳሌ:- አንቀልቀለ-ተነዋወጠ፣ አነዋወጠ ይላል።
የንባብ አደራራጊ የትርጓሜ አድራጊ፣ አስደራጊ፣ ተደራጊ፣ አደራራጊ አለ። ለምሳሌ አስተርአየ-ታየ፣ አሳየ ይላል።
የንባብ ተደራራጊ የትርጓሜ ተደራጊ አለ። ምሳሌ ተጋብአ-ተሰበሰበ ይላል።
የተገብሮ አመል በንባባቸውም በትርጓሜያቸውም የማይገኝባቸው አራት ናቸው። እነዚህም “ከብረ፣ ነግሠ፣ ሞተ፣ ቆመ” ናቸው። እነዚህም ዘራቸውን ይስባሉ እንጂ ከሌላ ነገር ገብተው አይስቡም። ከብረ ክብረ፣ ነግሠ ንግሠ፣ ቆመ ቆመ፣ ሞተ ሞተ ይላል። ምሥጢራቸው ግን ተደራጊ ነው።
በፍጹም ገቢራቸው በውድ ሁለት በግድ አንድ፣ በተገብሯቸው በውድ አንድ የሚስቡ ግሦች አሉ። እነዚም ላጸየ-ላጨ፣ መተረ-ቆረጠ፣ ረገዘ-ወጋ፣ ሐነቀ-አነቀ፣ ኰርዐ-መታ ናቸው። በውድ ሁለት ሲስቡ ላጸየ ሕፃነ ርእሶ ይላል፤ ትርጉሙ ሕፃኑን ራሱን ላጨ ይላል። አሕዛብ መተርዎ ለዮሐንስ ክሣዶ ይላል፤ ትርጉም አሕዛብ የዮሐንስ አንገቱን ቆረጡት ማለት ነው። አይሁድ ረገዝዎ ለክርስቶስ ገቦሁ ይላል ትርጉሙ አይሁድ የክርስቶስን ጎኑን ወጉት ይላል። ተደራጊዎቻቸው በውድ አንድ ሲስቡ ሕፃን ተላጸየ ርእሶ ይላል ትርጉሙ ሕፃን ራሱን ተላጨ ማለት ነው።
አሥራወ ቀለማት በአሉታ ጊዜ በአስደራጊ በአደራራጊ ከቀዳማይ ይወጣሉ። ሲወጡም ሁለት “አ” ቢገኝ አንዱን፣ አንድ “አ” ቢገኝ ያንኑ ያስለቅቁታል። ከሁለቱ “አ” አንዱን “አ” ሲያስለቅቁ ‘አእመረ-አወቀ’ ለሚለው አሉታው ‘ኢያእመረ-አላወቀም’ ነው። አንዱን ‘አ’ ሲያስለቅቁ “አፍቀረ-ወደደ” ለሚለው አሉታው “ኢያፍቀረ-አልወደደም” የሚለው ነው።
በእርባታ ጊዜ “ተ” ን ውጠው የሚያስቀሩ ቀለማት ስድስት ናቸው እነዚህም “ሰ፣ተ፣ዘ፣ደ፣ጠ፣ጸ” ናቸው። ተሰብሐ-ተመሰገነ ብሎ ይሴባሕ-ይመሰገናል፣ ይሰባሕ-ይመሰገን ዘንድ፣ ይሰባሕ-ይመስገን ይላል። ተጠምቀ-ተጠመቀ ብሎ ይጠመቅ-ይጠመቃል፣ ይጠመቅ-ይጠመቅ ዘንድ፣ ይጠመቅ-ይጠመቅ ይላል። ተደንገለ-ተጠበቀ ብሎ ይደነገል-ይጠበቃል፣ ይደንገል-ይጠበቅ ዘንው፣ ይደንገል-ይጠበቅ ይላል። ተተርአሰ-ተንተራሰ ብሎ ይተረአስ-ይንተራሳል፣ ይተርአስ-ይንተራስ ዘንድ፣ ይተርአስ-ይንተራስ ይላል። ተጸምደ-አገለገለ፣ ይጸመድ-ያገለግላል፣ ይጸመድ-ያገለግል ዘንድ፣ ይጸመድ-ያገልግል ይላል። ተዘምደ-ዘመድ ሆነ፣ ይዘመድ-ዘመድ ይሆናል፣ ይዘመድ-ዘመድ ይሆን ዘንድ፣ ይዘመድ-ዘመድ ይሁን ይላል። ነገር ግን ይህን ሕግ የማይጠብቁ ሁለት ግሦች አሉ እኒህም ተስዐ-ዘጠኝ አደረገ የሚለውና ተስዕዐ-ተገፈፈ የሚሉት ናቸው። አረባባቸውም ተስዐ ብሎ ይቴስዕ፣ ይተስዕ፣ ይተስዕ ይላል። ተሥዕዐ ብሎ ይትሰዐዕ፣ ይትሰዐዕ፣ ይትሰዐዕ ይላል።
ንዑስ አንቀጻቸውና ሳድስ ቅጽላቸው አንድ የሚሆኑ ግሦች አሉ። እኒህን ርኅበ-ተራበ፣ ጸበ-ጠበበ፣ ቀለ-ቀለለ፣ መረ-መረረ፣ ኖኀ-ረዘመ፣ መፀ-ቦካ(ኾመጠጠ) ናቸው። ሲነገሩም ርኅበ ካለው ርኂብ ርኂቦት ይወጣል። ሳድስ ቅጽሉ ርኂብ፣ ርኂባን፣ ረኃብ፣ ረኃባት ይላል። የቀለ ንዑስ አንቀጽ ቀሊል ቀሊሎት ነው። ሳድስ ቅጽሉ ቀሊል፣ ቀሊላን፣ ቀላል፣ ቀላላት ይላል። የጸበ ንዑስ አንቀጽ ጸቢብ ጸቢቦት ነው። ሳድስ ቅጽሉ ጸቢብ፣ ጸቢባን፣ ጸባብ፣ ጸባባት ይላል። የመሪር ንዑስ አንቀጹ መሪር መሪሮት ነው። ሳድስ ቅጽሉ መሪር፣ መሪራን፣ መራር፣ መራራት ይላል። የኖኀ ንዑስ አንቀጽ ነዊኅ ነዊኆት ይላል። ሳድስ ቅጽሉ ነዊኅ፣ ነዊኃን፣ ነዋኅ፣ ነዋኃት ይላል። የመፀ ንዑስ አንቀጽ መፂፅ መፂፆት ነው። ሳድስ ቅጽሉ መፂፅ፣ መፂፃን፣ መፃፅ፣ መፃፃት ይላል። ሌሎችም እኒህን መስለው የሚሄዱ አሉ ለምሳሌ ጸልመ-ጨለመ ንዑስ አንቀጹ ጸሊም ጸሊሞት ነው። ሳድስ ቅጽሉ ጸሊም፣ ጸሊማን፣ ጸላም፣ ጸላማት ይላል። ረሥአ-ረሳ ንዑስ አንቀጹ ረሢእ ረሢኦት ይላል። ሳድስ ቅጽሉ ረሢእ፣ ረሢኣን፣ ረሣእ፣ ረሣኣት ይላል። ጠበ-ብልሀተኛ ሆነ ለሚለው ንዑስ አንቀጹ አንቀጹ ጠቢብ ጠቢቦት ይላል። ሳድስ ቅጽሉ ጠቢብ፣ ጠቢባን፣ ጠባብ፣ ጠባባት ይላል። ከላይ ያየናቸው ከዚህ ያየናቸው በሙሉ ንዑስ አንቀጻቸው ላልቶ ይነበባል። ሳድስ ቅጽላቸው የሴቶች ጠብቆ ይነበባል። ከወንዶችም ጸሊም፣ ጸሊማን እና ነዊኅ፣ ነዊኃን ይጠብቃሉ።
በ”ወ” ለደረሰ ግሥ በ”ተ” ካልተነሳ በራሱ ካልተገሰሰ በመድረሻው ሳድስ ቀለም ከካልዓይ ከአንድ ከትእዛዝ የለውም። ካዕብ ነው እንጂ ሳድስ ቀለም ሲታጣ አርኀወ-ከፈተ፣ ያርኁ-ይከፍታል፣ ያርኁ-ይከፍት ዘንድ፣ ያርኁ- ይክፈት ይላል። በ”ተ” ሲነሳ ግን አለው። ይህም ተኄረወ-ቸር ሆነ፣ ይትኄረው-ቸር ይሆናል፣ ይትኄረው-ቸር ይሆን ዘንድ፣ ይትኄረው-ቸር ይሁን ይላል። በራሱ ሲገሰስ ከወወ-ቅልጥፍጥፍ አለ፣ ይከውው-ቅልጥፍጥፍ ይላል፣ ይክውው-ቅልጥፍጥፍ ይል ዘንድ፣ ይክውው-ቅልጥፍጥፍ ይበል ይላል። የሴቲቱ ሳድስ ቅጽል ግን ሳድሱን አስለቅቆ ካዕብ አድርጎ ይነገራል ሲነገርም ከተሠርገወ ሥርጉት፣ ከደለወ ድሉት ይወጣል።
በ”የ” ለደረሰ ግሥ በ”ተ” ካልተነሳ በራሱ ካልተገሰሰ መድረሻው በካልዓይ ሳድስ የለውም። ሣልስ ነው እንጂ። ሳድስ ሲታጣም ኀለየ-አሰበ፣ ይኄሊ-ያስባል፣ ርእየ-አየ፣ ይሬኢ-ያያል ይላል። በ’ተ’ ሲነሳ ተኀሥየ-ተደሰተ፣ ይትኀሠይ-ይደሰታል ይላል። በራሱ ሲገስስ ጸማሕየየ-ጠወለገ፣ ይጸማሐይይ-ይጠወልጋል፣ ይጸማሕይይ-ይጠወልግ ዘንድ፣ ይጸማሕይይ-ይጠውልግ ይላል። በ”የ” በንዑስ አንቀጹና በቦዙ መካከል ሳድስ ቀለም እንጂ ሣልስ ቀለም አይገኝም ሲነገርም ርእይ ርእዮት-ማየት፣ ጸግይ ጸግዮት-ማበብ ይላል። ርእዮ-አይቶ፣ ጸግዮ-አብቦ ይላል።
በግሱ ሁሉ “ሀ” እና “አ” በመካከል ሲገኙ የሚቀድሟቸውን ቀለማት በቀዳማይ ግእዝ፣ራብዕ፣ሳድስ ያደርጋሉ። ለምሳሌ ተልዕለ፣ ተልዐለ፣ ተለዐለ፣ ተላዐለ፣ ተላዕለ ብሎ ከፍ ከፍ አለ ይላል። በአምስት መንገድ ይሄዳል። በሁለት መንገድ የሚሄድም አለ። ምሳሌ:-ወዐለ፣ ዋዐለ ብሎ ዋለ ይላል።
ከአራት ቀለም በላይ ያለ ግስ ሁሉ የንዑስ አንቀጹ መካከሉ ሳድስ መድረሻው ሳብዕ ይሆናል። ምሳሌ አንቀልቀለ-ተነዋወጠ ይልና አንቀልቅሎ አንቀልቅሎት-መነዋወጥ ይላል። ሦስትም አራትም ቀለም የሆነ ግሥ በራብዕ፣ በኃምስ፣ በሳብዕ ሲነሳ እንዲሁ ነው። ምሳሌ ሌለየ-ለየ ብሎ ሌልዮ ሌልዮት-መለየት ይላል። ሁለትም ሦስትም ቀለም ለሆነ ግስ የንዑስ አንቀጹ መካከሉ ሣልስ መድረሻው ሳድስ ነው። ምሳሌ ሖረ-ሄደ ብሎ ሐዊር ሐዊሮት መግደል ይላል። ክህለ-ቻለ ብሎ ክሂል ክሂሎት መቻል ይላል።
በውስጥ ማሰሪያ የሚያወጡ አገባባት ፲፪ ናቸው። እኒህም በ፣ ውስተ፣ ለ፣ እስከ፣ ምስለ፣ እም፣ መንገለ፣ ቅድመ፣ ድኅረ፣ ዘ፣ ከመ እና ኀበ ናቸው። በ ሲያስር እግዚአብሔር በሰማይ ብሎ እግዚአብሔር በሰማይ አለ ይላል። “ውስተ” ሲያስር ንጉሥ ውስተ ጽርሑ ብሎ ንጉሥ በአዳራሹ ውስጥ አለ ይላል። እስከ ሲያስር ሄኖክ ወኤልያስ እስከ ይእዜ በገነት ብሎ ሄኖክና ኤልያስ በገነት እስከዛሬ አሉ ይላል። ምስለ ሲያስር ማርያም አመ ወረደት ግብፀ ምስለ ዮሴፍ ወሰሎሜ ብሎ ማርያም ወደ ግብጽ በወረደች ጊዜ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ነበረች። ቅድመና ድኅረ ሲያስሩ አመ ገብኡ ኢሎፍሊ ኢዮአብ ወአቢሳ ቅድመ/ድኅረ ዳዊት ብሎ ኢሎፍላውያን በተመለሱ ጊዜ ኢዮአብና አቢሳ በዳዊት ፊት/ኋላ ነበሩ ይላል። ለ ሲያስር ስብሐት ለአብ ብሎ ለአብ ምስጋና ይገባል ይላል። ዘ ሲያስር አምላክ ዘእማርያም ብሎ አምላክ ከማርያም የተገኘ ነው ይላል። ከመ ሲያስር ሚካኤል ዘከመ አምላኩ ለርኅራኄ ብሎ ሚካኤል ለርኅራኄ እንደ አምላኩ ነው ይላል።
ነባር አናቅጽ እንደ ዐበይት አናቅጽ እየተዘረዘሩ በሙሻ ዘር የሚወጡ አገባባትን ሁሉ ያወጣሉ። ሃይማኖት ቦቱ ለጊዮርጊስ ለእርሱ ለጊዮርጊስ ሃይማኖት አለው ይላል። ሎቱ እንደወጣ አስተውል። እምኔሁ ሲወጣ ሃይማኖት አልቦቱ ለንስጥሮስ ይላል፡፡ ትርጉሙ ከእርሱ ለንስጥሮስ ሃይማኖት የለውም ይላል። እንበለ ሲወጣ ክህደት አልቦቱ ለዲያብሎስ ይላል ትርጉሙ ያለ እርሱ ለዲያብሎስ ክህደት የለውም ማለት ነው። በእንቲኣሁ ሲወጣ አምላክ ቦቱ ለሙሴ በታቦር ይላል ትርጉሙ ስለእርሱ በታቦር ለሙሴ አምላክ አለው ይላል። እስከኔሆሙ ሲወጣ አምላክ ቦቶሙ ለአድማስ ወለናጌብ ይላል ትርጉሙ እስከ እነርሱ ለአድማስና ለናጌብ አምላክ አላቸው ይላል። ምስሌሁ ሲወጣ ዕዝራ ቦቱ ለሄኖክ በገነት ይላል ትርጉሙ ከእርሱ ጋራ በገነት ለሄኖክ ዕዝራ አለው ይላል።
ንዑሳን አናቅጽ ሳቢ ከተሳቢ ዘርፍ ከባለቤት እየተናበቡ ፳፭ አገባባትን ያወጣሉ። አገባባቱም ለ፣ በ፣ በእንተ፣ ምስለ፣ ከመ፣ ኀበ፣ እስከ፣ እም፣ እንበለ፣ ግእዝ፣ ውስተ፣ ማእከለ፣ ላዕለ፣ ታሕተ፣ የማነ፣ ጸጋመ፣ ኀበ፣ መንገለ፣ ወእደ ዘንድ ሲሆኑ፣ መጠነ፣ ጊዜ፣ ለለ፣ በበ፣ ዘዘ፣ ድኅረ፣ ቅድመ እና “ኢ” ሆኖ ሲሆን ናቸው። ዐሥሩን ከሙሻ ዘርፍ አይተናል። ቀሪዎቹን ቀጥለን እናሳያለን። ድኅረ ሲገባ አፍቀረ አማኑኤል ዳዊት ንግሠተ ሐማ ሳኦል ይላል ትርጉሙ ከሐማ ሳኦል በኋላ መንገሥን አማኑኤል ዳዊት ወደደ ይላል። መጠነ ሲገባ አፍቀረ አማኑኤል ሰሎሞን ንግሠተ ሐማ ዳዊት ይላል ትርጉሙ የሐማ ዳዊትን ያህል መንገሥን አማኑኤል ሰሎሞን ወደደ ይላል። ቅድመ ሲገባ ፈተወ ሐማ ሳኦል ንግሠተ አማኑኤል ዳዊት ይላል ትርጉሙ ከአማኑኤል ዳዊት በፊት መንገሥን ሐማ ሳኦል ወደደ ይላል።
ላዕለ ሲገባ ገብረ አማኑኤል ስቅለተ መስቀል ይላል ትርጉሙ በመስቀል ላይ መሰቀልን አማኑኤል ወደደ። ታሕተ ሲገባ አፍቀረ ገብር ንብረተ እግዚኡ ይላል ትርጉሙ ከጌታው በታች መቀመጥን አገልጋይ ወደደ። ማእከለ ሲገባ ሠምረ አብ አማኑኤል ንብረተ ፈያት አበው ይላል ትርጉሙ ከአባቶች ሽፍቶች ጋር መቀመጥን አማኑኤል አባት ወደደ ይላል። በንዑስ አንቀጽም በአምስቱ አእማድ ይህንኑ መስሎ ይሄዳል። ምሳሌ ጸጋመ ሲገባ ለኃጥአን ቀዊመ አምላክ ይላል ትርጉሙ በአምላክ ግራ መቆም ለኃጥኣን ይገባል ማለት ነው። ጊዜ ሲገባ አፍቀረ ጲላጦስ አስተቃትሎተ ቀትር አምላከ ምስለ ፈያት ይላል ትርጉሙ ከሽፍቶች ጋር አምላክን በቀትር ጊዜ ማገዳደልን ጲላጦስ ወደደ ይላል። በሳድስ ቅጽል ሲገባ ምሳሌ የማነ ሲገባ ወልድ ንቡረ አብ ይላል ትርጉሙ በአብ ቀኝ የተቀመጠ ወልድ ማለት ነው። ኢ ሲገባ አምላክ ምውተ ሰብእ ይላል ትርጉሙ ሰው ሆኖ የሞተ አምላክ ማለት ነው።
“እም” በዘንድ ሲወድቅ ሕጸቱ እንጂ ምልአቱ አይስማማውም። ይህም እምይብላዕ ይላል እንጂ እምነ ይብላዕ አይልም። እስከም እንዲሁ ነው።
አገባባት ሁሉ ከዘር፣ ከነባር፣ ከስም፣ ከግብር እየተናበቡ አዋጅ አያፈርሱም። “እም” ብቻ ያፈርሳል። ሲያፈርስም በሳድስ እየተናበበ ነው። ምሳሌ እምድር ይላል። “ሰ” ቀለም ይለውጣል። ሲለውጥም አነ ያለውን አንሰ ይላል።
አገባብ ሲዘረዝር ራሱን ወደ ሣልስ ወደ ራብዕ ወደ ኀምስ እየመለሰ ይዘረዝራል። “እንተ፣ዘ፣እለ” ራሳቸውን ወደ ሣልስ እየመለሱ ባዕድ ቀለም “ኣ”ን ያመጣሉ። ሲገቡም ዚኣሁ፣ እንቲኣሁ፣ እሊኣሁ ይላል። እንዲህ እያለ በዐሥሩም መራሕያን ይዘረዘራል።
ከመ ከአገባባት ተለይቶ በገቢር አንቀጽ ይሳባል ሲሳብም በዐቢይነቱ ነው። ምሳሌ ተነበዩ ነቢያት ከመ ይመጽእ ክርስቶስ ይላል። ነቢያት ክርስቶስ እንደሚመጣ ተነበዩ (ተናገሩ) ማለት ነው። ተነበዩ ተሳቢ ያስፈልገው ነበር ‘ከመ’ ስላለ ግን ተሳቢ እንደቀረ አስተውል። የሚስቡት አናቅጽ ሰባት ናቸው። እነዚህም ተነበየ፣ ሰበከ፣ አእመረ፣ ጠየቀ፣ ሰምዐ፣ ገብረ እና ለበወ ናቸው።
ከነባር አናቅጽ ለከመ ውእቱን ይዞም ሳይዝም አፍዛዥነት ያላቸው ሳቢዎች አሉት። እኒህም እንጋ፣ እንዳኢ ናቸው። ሲገቡ ‘ከመ’ ባለቤት ይሆናል። ምሳሌ እንጋ/እንዳኢ ከመ ብዕለ ሰብእ እስመ ይሜሕር ነዳየ ወምስኪነ ይላል ትርጉሙ ሰው ባዕለ ጸጋ እንደሆነ እንጃ ለነዳይና ለምስኪን ይመጸውታልና ይላል። በዚህ ጊዜ ባለቤቱ “ከመ” ነው። ሰብእ የማንጸሪያ ባለቤት ነው። “እመ”ም እንደ ከመ ይገባል። ንጉሥ እመቦ በመንበሩ ንቅንት ሎቱ ይላል ትርጉሙ ንጉሥ በወንበሩ ካለ እንታጠቅለት ይላል። ንጉሥ የማንፀሪያ ባለቤት እመ የዓረፍተ ነገሩ ባለቤት ነው።
“ወ” በትእዛዝና በትእዛዝ መካከል ገብቶ “ና” ይሆናል። ተንሥእ ወሑር ሲል ተነሥና ሂድ ማለት ነው።
‘ሁ፣ኑ፣እንጋ’ ወይ፣ን ይሆናሉ። “ሁ” እመን ሶበን ይዞ ይነገራል። “ኑ” በስምና በእርባ መካከል ይነገራል። “እንጋ” ሁን ምን ይከተላል። ሲገቡም ዘመጽኡ ሰብአ ሰገል ሶበሁ ተወልደ ክርስቶስ ይላል ትርጉሙ ሰብአ ሰገል የመጡ ክርስቶስ ቢወለድ ነውን? /ነው ወይ? ይላል። ተወልደኑ እንጋ ይላል ትርጉሙ ተወልዶ ይሆንን ይላል።
ዘንድ አንቀጽ ‘ከመ’ን ይዞ ሳይዝም መፍትው፣ ድሎት፣ ጽድቅ፣ ፍትሕ፣ ርትዕ፣ ሥርዐት፣ ኩነት፣ ርቱዕ በማሰሪያነት ሲነገሩ ባለቤት ይሆናል። ምሳሌ መፍትው ከመ ያድኅኖ ለአዳም አምላክ ይላል ትርጉሙ አምላክ አዳምን ያድነው ዘንድ ይገባል ይላል። ያድኅኖ የዓረፍተ ነገሩ ባለቤት ነው። አምላክ የዘንድ ባለቤት ነው።
Read More
ነገረ ግሥ
መሣግር:– መሣግር የሚባለው በዝርዝር ጊዜ ካልአይ አንቀጹን የቀተለን ወደ ቀደሰ፣ የቀደሰን ወደ ቀተለ፣ የገብረን ወደ ሰብሐ፣ የሰብሐን ወደ ገብረ፣ የክህለን ወደ ቀደሰ እየለዋወጠ የሚዘረዝር ማለት ነው። መሣግር የሚሆኑ ፊደላት “ሀ፣ ረ፣ አ፣ ወ፣ ዘ” ናቸው።
Read Full Story