በዚህ ምክንያት ‹‹በጎውን ማን ያሳየናል የሚሉ ብዙዎች ናቸው›› ማለታቸው እውነት ነው፡፡ ይህ ጨለምተኝነት አይደለም፤ ይህ ሁሉንም የመደምሰስ የቀቢጸ ተስፋ ንግግርም አይደለም፡፡ እውነታ ነው፡፡
‹‹በሽታውን የደበቀ መድኃኒት የለውም›› እንዲሉ አበው በጎውን የሚያሳዩን፣ የበጎነት መምህራን፣ የበጎነት አብነቶች፣ በጎ መሪዎችን፣ በጎ መምህራንን፣ በጎ ወላጆችን፣ በጎ ሽማግሌዎችን መፍጠር የሚያስችል ንግግርና ውይይት ያስፈልጋል፡፡
“ሰማይ አይታረስ ንጉሥ አይከሰስ” የሚሉት ዓይነት ብሂል ያለ ቦታው እየጠቀስን፣ አባቶቻችን፣ መሪዎቻችን፣ ወላጆቻችን፣ ሽማግሌዎቻችን ሁሉ ችግራቸውን ቆም ብለው እንዳያዩ፣ የሚመሩትን ሕዝብ ችግር እንዳይመለከቱ፣ ራሳቸውንም፣ መንጋውንም እንዳይታደጉ የሚያደርግ፣ ማክበር የሚመስል ግን ደግሞ ነገን የዘነጋ ተሸኮርማሚነት የትም አላደረሰንም፡፡
ይልቁንስ ‹‹በልቡ ቅንንት ጠበቃቸው፤ በእጁም ብልህነት መራቸው›› እንዳለ ቅዱስ ዳዊት ቅንነትና ብልህነት ያልተለያቸው መሪዎች እንዲኖሩን፣ ያሉትም የበጎነት ተምሳሌት ሆነው በጎውን የሚያሳዩ፣ በጎ መሪዎች እንዲሆኑ በግልጥ መነጋገር፣ መወያየት፣ የመፍትሔ ሐሳብ ማመንጨት ይገባል፡፡ (መዝ.፸፯፥፸፪)
Hi, this is a comment.
To get started with moderating, editing, and deleting comments, please visit the Comments screen in the dashboard.
Commenter avatars come from Gravatar.