መንፈሳዊም ሥጋዊም ሥልጣን ከእግዚአብሔር

ቅዱስ ጴጥሮስ ለመሪዎች ይህንን ትልቅ ትእዛዝ መናገሩ መንፈሳዊም ሥጋዊም ሥልጣን ከእግዚአብሔር የሚገኝና የሥልጣኑም ዋና ዓላማ ሕዝብን ለመምራት፣ ለመጠበቅ፣ ለማገልገል ብሎም ለመመገብ ስለሆነ ነው፡፡

ምክንያቱም እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ንጉሡን ለሥጋዊ ፍርድ፣ ጥበቃና መግቦት ሲመርጠው ጳጳሱን ደግሞ ለመንፈሳዊ ፍርድ፣ ጥበቃና መግቦት የሾማቸው መሆኑን ያስረዳል፡፡ ይህንን ቸል ቢሉ ደግሞ ፍርድ እንደሚጠብቃቸው ያስረዳል፡፡

ተወዳጆች ‹‹በጎውን ማን ያሳየናል›› የሚሉ ድምጾች የበዙት ሥጋዊም መንፈሳዊም መሪዎች ስለሚያስፈልጋቸው ነው፡፡ ስለሆነ በጎውን የሚያሳዩን መሪዎች እንዲሰጠን እንጸልይ፤ እኛም በጎውን የሚያሳዩ መሪዎችን ለማምጣት እንምከር፡፡ እኛም በጎውን የምናይ ለመሆን እንትጋ!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

በጎነት ወይም በጎ ነገር

በጎነት ወይም በጎ ነገር ከመንፈስ ቅዱስ ነው፤ በጎው ነገር ሁሉ የሚገኘውም በአማኞች ሕይወት ውስጥ ነው ከተባለ አማኞች ነን የምንል እኛ ስንቶቻችን በጎነት አለን? ያለንን በጎነትስ ለማን አሳየን? በጎነትስ ካለን ይህ ሁሉ ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊ ፖለቲካዊና ኢከኖሚያዊ ምስቅልቅልስ ለምን ደረሰብን? ይህንንስ አምኖ የሚቀበልና ለችግሮች መፍትሔ ለመሆን የሚችል አካልስ ለምን ማግኘት ተሳነን? እንደነዚህ ያሉ ብዙ ጥቄዎች የሚያነሱ ግን ደግሞ መልስ ያጡ ብዙዎች    ናቸው፡፡

በጎውን የማሳየት ድርሻ የማን ነው?

በጎውን የማሳየት ድርሻ የሁላችንም ነው፡፡ ነገር ግን በጎውን ለማሳየት የተመረጡ፣ ተመርጠውም የተሾሙ መሪዎች ዋነኞቹ ናቸው፡፡መሪዎች ሲባል ብዙ ዓይነት መሪዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ የቤተሰብ መሪዎች፣ የማኅበረሰብ መሪዎች፣ የሀገር መሪዎች እንዲሁም ሃይማኖታዊ መሪዎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በልቡ ቅንነት

ይልቁንስ ‹‹በልቡ ቅንንት ጠበቃቸው፤ በእጁም ብልህነት መራቸው›› እንዳለ ቅዱስ ዳዊት ቅንነትና ብልህነት ያልተለያቸው መሪዎች እንዲኖሩን፣ ያሉትም የበጎነት ተምሳሌት ሆነው በጎውን የሚያሳዩ፣ በጎ መሪዎች እንዲሆኑ በግልጥ መነጋገር፣ መወያየት፣ የመፍትሔ ሐሳብ ማመንጨት ይገባል፡፡ (መዝ.፸፯፥፸፪)

ሕዝብ መሪን፣ መሪም ሕዝብን ይፈጥራልና መፍትሔ ስንሰጥ፣ በመከራችን እየቆዘምን፣ መሪዎቻችንን እየረገመምን መቀጠል የት ያደርሳል? ‹‹መሪ የሌላቸው ሕዝቦች እንደረገፉ ቅጠሎች፣ እንደተረበረቡ ግንዶች ናቸው›› እንደሚባለው ሕዝብ ያለመሪ ምንም ነውና መሪ እናዘጋጅ!

ለቤተሰቡ ቁንጮ የሆነ መልካም የቤተሰብ መሪ፣ በማኅበረሰቡ ዘንድ ቅቡልነት ያለው፣ የማንም ያልሆነ፣ የሁሉም የሆነ የማኅበረሰብ መሪ፣ ለወጣበት ጎሳ፣ ለሚናገረው ቋንቋ የማይወግን፣ አገልጋይ እንጅ ተገልጋይ ያልሆነ፣ የሕዝብና የሀገር መሪ ይኖረን ዘንድ እንትጋ!

በእጁም ብልህነት መራቸው

ቅዱስ ጴጥሮስ ንጉሡንና ጳጳሱን እንዲህ ይላቸዋል፡፡ ‹‹ንጉሥ ሆይ፥ አንተ ሥጋዊውን ሥራ ትጠብቃለህ፤ ስለዚህ አንተና ጳጳሱ የእግዚአብሔር በጎች እንዳይጠፉ ተግታችሁ ጸልዩ፤….መንጋዎቻችሁን ጠብቁ፤ ይህንንም ቃል እየሰማችሁ ለመጠበቅ ትጉ፡፡ የእግዚአብሔርን መግቦት ቸል አትበሉ፡፡ እናንተን የሚመግብ እርሱ ነውና መጋቢነታችሁን ችላ አትበሉ፡፡›› (ቀሌምን. ፱፥፹፬ እና ፹፭)