መንፈሳዊም ሥጋዊም ሥልጣን ከእግዚአብሔር

ቅዱስ ጴጥሮስ ለመሪዎች ይህንን ትልቅ ትእዛዝ መናገሩ መንፈሳዊም ሥጋዊም ሥልጣን ከእግዚአብሔር የሚገኝና የሥልጣኑም ዋና ዓላማ ሕዝብን ለመምራት፣ ለመጠበቅ፣ ለማገልገል ብሎም ለመመገብ ስለሆነ ነው፡፡

ምክንያቱም እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ንጉሡን ለሥጋዊ ፍርድ፣ ጥበቃና መግቦት ሲመርጠው ጳጳሱን ደግሞ ለመንፈሳዊ ፍርድ፣ ጥበቃና መግቦት የሾማቸው መሆኑን ያስረዳል፡፡ ይህንን ቸል ቢሉ ደግሞ ፍርድ እንደሚጠብቃቸው ያስረዳል፡፡

ተወዳጆች ‹‹በጎውን ማን ያሳየናል›› የሚሉ ድምጾች የበዙት ሥጋዊም መንፈሳዊም መሪዎች ስለሚያስፈልጋቸው ነው፡፡ ስለሆነ በጎውን የሚያሳዩን መሪዎች እንዲሰጠን እንጸልይ፤ እኛም በጎውን የሚያሳዩ መሪዎችን ለማምጣት እንምከር፡፡ እኛም በጎውን የምናይ ለመሆን እንትጋ!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

በጎነት ወይም በጎ ነገር

በጎነት ወይም በጎ ነገር ከመንፈስ ቅዱስ ነው፤ በጎው ነገር ሁሉ የሚገኘውም በአማኞች ሕይወት ውስጥ ነው ከተባለ አማኞች ነን የምንል እኛ ስንቶቻችን በጎነት አለን? ያለንን በጎነትስ ለማን አሳየን? በጎነትስ ካለን ይህ ሁሉ ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊ ፖለቲካዊና ኢከኖሚያዊ ምስቅልቅልስ ለምን ደረሰብን? ይህንንስ አምኖ የሚቀበልና ለችግሮች መፍትሔ ለመሆን የሚችል አካልስ ለምን ማግኘት ተሳነን? እንደነዚህ ያሉ ብዙ ጥቄዎች የሚያነሱ ግን ደግሞ መልስ ያጡ ብዙዎች    ናቸው፡፡

በጎውን የማሳየት ድርሻ የማን ነው?

በጎውን የማሳየት ድርሻ የሁላችንም ነው፡፡ ነገር ግን በጎውን ለማሳየት የተመረጡ፣ ተመርጠውም የተሾሙ መሪዎች ዋነኞቹ ናቸው፡፡መሪዎች ሲባል ብዙ ዓይነት መሪዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ የቤተሰብ መሪዎች፣ የማኅበረሰብ መሪዎች፣ የሀገር መሪዎች እንዲሁም ሃይማኖታዊ መሪዎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በልቡ ቅንነት

ይልቁንስ ‹‹በልቡ ቅንንት ጠበቃቸው፤ በእጁም ብልህነት መራቸው›› እንዳለ ቅዱስ ዳዊት ቅንነትና ብልህነት ያልተለያቸው መሪዎች እንዲኖሩን፣ ያሉትም የበጎነት ተምሳሌት ሆነው በጎውን የሚያሳዩ፣ በጎ መሪዎች እንዲሆኑ በግልጥ መነጋገር፣ መወያየት፣ የመፍትሔ ሐሳብ ማመንጨት ይገባል፡፡ (መዝ.፸፯፥፸፪)

ሕዝብ መሪን፣ መሪም ሕዝብን ይፈጥራልና መፍትሔ ስንሰጥ፣ በመከራችን እየቆዘምን፣ መሪዎቻችንን እየረገመምን መቀጠል የት ያደርሳል? ‹‹መሪ የሌላቸው ሕዝቦች እንደረገፉ ቅጠሎች፣ እንደተረበረቡ ግንዶች ናቸው›› እንደሚባለው ሕዝብ ያለመሪ ምንም ነውና መሪ እናዘጋጅ!

ለቤተሰቡ ቁንጮ የሆነ መልካም የቤተሰብ መሪ፣ በማኅበረሰቡ ዘንድ ቅቡልነት ያለው፣ የማንም ያልሆነ፣ የሁሉም የሆነ የማኅበረሰብ መሪ፣ ለወጣበት ጎሳ፣ ለሚናገረው ቋንቋ የማይወግን፣ አገልጋይ እንጅ ተገልጋይ ያልሆነ፣ የሕዝብና የሀገር መሪ ይኖረን ዘንድ እንትጋ!

በእጁም ብልህነት መራቸው

ቅዱስ ጴጥሮስ ንጉሡንና ጳጳሱን እንዲህ ይላቸዋል፡፡ ‹‹ንጉሥ ሆይ፥ አንተ ሥጋዊውን ሥራ ትጠብቃለህ፤ ስለዚህ አንተና ጳጳሱ የእግዚአብሔር በጎች እንዳይጠፉ ተግታችሁ ጸልዩ፤….መንጋዎቻችሁን ጠብቁ፤ ይህንንም ቃል እየሰማችሁ ለመጠበቅ ትጉ፡፡ የእግዚአብሔርን መግቦት ቸል አትበሉ፡፡ እናንተን የሚመግብ እርሱ ነውና መጋቢነታችሁን ችላ አትበሉ፡፡›› (ቀሌምን. ፱፥፹፬ እና ፹፭)

ቅዱስ ጴጥሮስ ለመሪዎች ይህንን ትልቅ ትእዛዝ መናገሩ መንፈሳዊም ሥጋዊም ሥልጣን ከእግዚአብሔር የሚገኝና የሥልጣኑም ዋና ዓላማ ሕዝብን ለመምራት፣ ለመጠበቅ፣ ለማገልገል ብሎም ለመመገብ ስለሆነ ነው፡፡

ምክንያቱም እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ንጉሡን ለሥጋዊ ፍርድ፣ ጥበቃና መግቦት ሲመርጠው ጳጳሱን ደግሞ ለመንፈሳዊ ፍርድ፣ ጥበቃና መግቦት የሾማቸው መሆኑን ያስረዳል፡፡ ይህንን ቸል ቢሉ ደግሞ ፍርድ እንደሚጠብቃቸው ያስረዳል፡፡

ተወዳጆች ‹‹በጎውን ማን ያሳየናል›› የሚሉ ድምጾች የበዙት ሥጋዊም መንፈሳዊም መሪዎች ስለሚያስፈልጋቸው ነው፡፡ ስለሆነ በጎውን የሚያሳዩን መሪዎች እንዲሰጠን እንጸልይ፤ እኛም በጎውን የሚያሳዩ መሪዎችን ለማምጣት እንምከር፡፡ እኛም በጎውን የምናይ ለመሆን እንትጋ!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

‹‹በጎውን ማን ያሳየናል››

ዲያቆን ይትባረክ መለሰ

ጥቅምት ፳፪፤፳፻፲፯  ዓመተ ምሕረት

እንደዚህ እንደኛ ያለ ክፉ ዘመን የገጠማቸው፣ መጥፎውን ትቶ በጎውን፣ ጠማማውን ሳይሆን ቀናውን፣ የጨለማውን ሳይሆን የብርሃኑን ጎዳና የሚያሳያቸው፣ የሚነግራቸውና የሚያስተምራቸው ያጡ፣ ግራ የተጋቡ ሕዝቦችን የተመለከተበትን ነገር እየነገረን ይመስላል ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ነው ይህንን ኃይለ ቃል የነገረን፡፡ ነቢዩ በዘመኑ፡-

ነቢይ ነውና አስቀድሞ ዛሬ ላይ እኛ እየገጠመን ያለውን ችግር ማለትም በጎውን የሚናገር፣ በጎውን የሚያደርግ፣ በጎን የሚያሳይ ያጣን ብዙዎች መሆናችንን የእኛን ሕይወት ቀድሞ ታይቶት የነገረንም ነው፡፡

በዘመናችን ብዙዎች ግራ ተጋብተዋል፤ የቀናው መንገድ በጎው ነገር ሁሉ ጠፍቶባቸዋል፤የተሻለውን, የሚጠቅመውን ዕረፍት ሰላም የሚሰጠውን, በጎውን ሁሉ የሚያሳይ በማጣት የሚሠቃዩ ‹‹በጎውን ማን ያሳየናል?›› እያሉ ያለ ዕረፍት ይጮኻሉ፡፡

ለመሆኑ በጎ ምንድን ነው? የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት በጎ የሚባለው ‹‹ማንኛውም መልካምና ጥሩ ሥራ›› እንደሆነ ይናገርና “በአማኞች ሕይወት ውስጥ የሚገኝ፣ እርሱም ከመንፈስ ቅዱስ የሆነ እንደሆነ፣ ሰዎችም የእግዚአብሔር ልጆች መሆናቸውን የሚገልጹበት መሆኑን ያትታል፡፡ በተጨማሪም የበጎነት ምንጭ እግዚአብሔር መሆኑን ይጠቅሳል፡፡” (መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃለት፣ ገጽ ፻፲፪)

በጎውን የማሳየት ድርሻ የማን ነው?

የማኅበረሰብ መሪዎች፡- ከቤተሰብ ያለፈውን ችግር የሚፈቱ የማኅበረሰቡን ሸክም የሚያቀልሉ፣የተጣላ የሚያስታርቁ፣ ያጠፋውን የሚቀጡ፣ የተቀማውን የሚያስመልሱ፣ የተበደለን የሚያስክሱ፣ የተፈሩ፣ የታፈሩ፣  እንደ ዋርካ የሰፉ፣ እንደ ችብሀ የለመለሙ፣ የሁሉ ማረፊያ ጥላ የሆኑ፣ በጎውን የሚያሳዩ፣ የበጎነት ተምሳሌቶች፣ የማኅበረሰብ መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ነበሩ፡፡

የሕዝብ መሪዎች፡- ከማኅበረሰብ መሪዎች ሲያልፍ “ዳኝነት፣ ቀና እና እውነተኛ ፍርድ፣ የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው” ብለው የሚያምኑ፣ የሙያ ግዴታቸውን የሚወጡ፣ ፍርድ እንዳይጎደል፣ ድሃ እንዳይበደል፣ ሕጉን ሥርዓቱን የሚጠብቁ የሚያስጠብቁ፣ የሚፈጽሙ፣ የሚያስፈጽሙ በጎውን ሁሉ የሚያሳዩ የሕዝብ መሪዎች ነበሩ፡፡

የሃይማኖት መሪዎች፡- ከሕዝብ መሪዎች ሲያልፍ፣ ፍትሕ ሲጓደል፣ ድሃ ሲበደል፣ ግፍ ሲበዛ፣ ሕዝብ ሲያዝን ደግሞ ሁሉንም የሚገዙ፣ ምግባራቸው የቀና፣ ሃይማኖታቸው የጸና፣ በሕዝቡና በእግዚአብሔር፣ በሕዝቡና በሌሎች መሪዎች መካከል የሚቆሙ፣ የደከመ የሚያርፍባቸው፣ ያዘነ የሚጽናናባቸው፣ የተሰበረን የሚጠግኑ፣ የተቆረጠን የሚቀጥሉ፣ ተስፋ ሥጋ ተስፋ ነፍስ የሚያጎናጽፉ፣ ፍርድ የማያጎድሎ፣ የሰው ፊት ዓይተው፣ የማያደሉ፣ ሥጋዊ ደማዊ ፍትወት የተወገደላቸው፣ ማለትም የገንዘብ ፍትወት፣ የዘረኝነት ፍትወት፣ የሹመት ፍትወት፣ ድል የተነሣላቸው፣ የሁሉም ለሁሉም የሆኑ፣ አጥር ደንበር የማይከልላቸው፣ ቅን ፈራጆች፣ በጎውን የሚያሳዩ  የሃይማኖት መሪዎች ነበሩ፡፡

የቤተሰብ መሪ

አሁን ግን ‹‹ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ መሪዎች›› እንደተባሉት ያሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ዓላማቸውን ረስተው፣ ለሕዝቡ በየወገናቸው ሸክም ሆነዋል፤ በምድራዊ ጥቅምና ክብር፣ ዝናና ምቾት ተጠምደዋል፡፡ (ማቴ.፳፫፥፳፫-፳፬)

ዕለት ዕለት በሕዝቡ ላይ ቀንበር ይጭኑበታል፤ ሸክም ያከብዱበታል፤ በጎች እረኛ አጥተዋል፤ በየቦታውም የሚያሰማራቸው፣ ከተኩላ ከቀበሮም የሚጠብቃቸው፣ በለመለመ መስክ፣ በምንጭ ውኃ የሚመግባቸው አጥተዋል፡፡ ምክንያቱም የመሪዎች ተልእኮ መምራት፣ መጠበቅ መመገብ ነውና፡፡

መልካሙን ሁሉ የሚያሳይ ወላጅ (የቤተሰብ መሪ) ሁሉ የሚፈራው፣ ሁሉ የሚያፍረው፣ ለሁሉ የሆነ፣ ከጎጥ ባሻገር፣ ከዘር ባሻገር ማየት የሚችል፣ ሁሉ የእኛ የሚለው የማኅበረሰብ መሪ አባት ሽማግሌ፣ “በሕዝቡ ላይ መሪ ዳኛ አገልጋይ አድርጎ የሾመኝ፣ የሀገሩ ባላደራ፣ የሕዝቡ አገልጋይ እኔ ነኝ፤ ሁሉም ሕዝብ የኔ ነው፤ እኔም የሁሉም ሕዝብ ነኝ፤ እግዚአብሔር  ያያል ፊት አይቸቼ ባደላ ይፈርድብኛል” የሚል የሕዝብ የፖለቲካ መሪ እየታጣ ነው፡፡

ከሁሉ የሚከፋው ግን ከዚህ ዓለም ክብር ይልቅ ለሚመጣው ሕይወት የሚተጉ ዓለምን ከነክፉ መሻቱ ገድለው ቀብረውታል ብለን የተከተልናቸው፣ በነፍስ በሥጋችን ላይ የተሾሙ፣ ለመንግሥተ እግዚአብሔር መንገድ ጠራጊ ያልናቸው፤ ‹‹ሥጋን ከክፉ መሻቱና ምኞቱ ጋር ስቀሉት›› ብለው ያስተማሩን ብዙዎች የሃይማኖት መሪዎች በሥጋ ክፉ መሻትና ምኞት ወድቀው ለሕዝቡ በረከት መሆናቸው ቀርቶ ዕዳ መሆናቸው ነው፡፡ (ገላ.፭፥፳፬)

በዚህ ምክንያት

በዚህ ምክንያት ‹‹በጎውን ማን ያሳየናል የሚሉ ብዙዎች ናቸው›› ማለታቸው እውነት ነው፡፡ ይህ ጨለምተኝነት አይደለም፤ ይህ ሁሉንም የመደምሰስ የቀቢጸ ተስፋ ንግግርም አይደለም፡፡ እውነታ  ነው፡፡

‹‹በሽታውን የደበቀ መድኃኒት የለውም›› እንዲሉ አበው በጎውን የሚያሳዩን፣ የበጎነት መምህራን፣ የበጎነት አብነቶች፣ በጎ መሪዎችን፣ በጎ መምህራንን፣ በጎ ወላጆችን፣ በጎ ሽማግሌዎችን መፍጠር የሚያስችል ንግግርና ውይይት ያስፈልጋል፡፡

“ሰማይ አይታረስ ንጉሥ አይከሰስ” የሚሉት ዓይነት ብሂል ያለ ቦታው እየጠቀስን፣ አባቶቻችን፣ መሪዎቻችን፣ ወላጆቻችን፣ ሽማግሌዎቻችን ሁሉ ችግራቸውን ቆም ብለው እንዳያዩ፣ የሚመሩትን ሕዝብ ችግር እንዳይመለከቱ፣ ራሳቸውንም፣ መንጋውንም እንዳይታደጉ የሚያደርግ፣ ማክበር የሚመስል ግን ደግሞ ነገን የዘነጋ ተሸኮርማሚነት የትም አላደረሰንም፡፡

ይልቁንስ ‹‹በልቡ ቅንንት ጠበቃቸው፤ በእጁም ብልህነት መራቸው›› እንዳለ ቅዱስ ዳዊት ቅንነትና ብልህነት ያልተለያቸው መሪዎች እንዲኖሩን፣ ያሉትም የበጎነት ተምሳሌት ሆነው በጎውን የሚያሳዩ፣ በጎ መሪዎች እንዲሆኑ በግልጥ መነጋገር፣ መወያየት፣ የመፍትሔ ሐሳብ ማመንጨት ይገባል፡፡ (መዝ.፸፯፥፸፪)